ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ለሀገር በቀል ዕውቀቶች ትኩረት ተሰጥቷል፦ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶር)
ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) በተገኙበት ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ የድጋፍ ሠልፍ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ተካሂደዋል ።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) እንደተናገሩት ብልፅግና ፓርቲ አካታች የሆነውን የፖለቲካ ስረዓት በመገንባት ሀገር በቀል ዕሳቤ በሆነው መደመር የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እየመለሰ የመጣ ነው ብለዋል።
ዞኑ ለልማትና ኢንቨስትመንት ምቹ ስነምህዳር ያለው መሆኑን ገልፀው በሀገር በቀል ዕሳቤ ሠላሙን መገንባት በመቻሉ የልማቱ ተጠቃሚ መሆን ችሏል ነው ያሉት።
ከመንግስት ተቋማት ጎን የባህላዊ አስተዳደር ሚና የጎላ መሆኑን ተናግረው ይህም የለውጡ መንግስት ቱሩፋቶች ናቸው ብለዋል።
በሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በማድረግ የህብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ ያሻሻሉና ክልሉ በራስ አቅም 60 በመቶ የምሆነውን በጀት መሸፈን መቻሉን ተናግረዋል።
ርዕሰ መስተዳደሩ አክለው ትላልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች በማጠናቀቅ አካባቢውን የኢኮኖሚና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ፓርቲው በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጽያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በሸካ ዞን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ተዋደውና ተከባብረው በህብረ ብሔራዊ አንድነት የሚኖርበት መሆኑን አስታውሰዋል ።
በለውጡ ሀገርቷን ከነበረችበት ውስብስብ ችግሮች በማላቀቀ በማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካ ዘርፈ ብዙ ውጤቶች መመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል ።
ፓርቲው ለዘመናት ተዘንግቶ የነበሩትን አካባቢዎች ትኩረት በመስጠት የመሠረተ ልማት ግንባዎችን እየተካሄደ መሆኑን ገልፀው በተቋም ግንባታ ረገድ በተከናወነ ስራም የድጂታል 2025ን በማሳካት 2030 ውጤታማ ለመሆን እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል ።
ኃላፊው አክለው ፓርቲው ሀገርቷ በኢ-ፍትሀዊ አካሄድ ያጣችውን የባህር በር ጥያቄ ለማስመለስ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው በ7ኛ ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ፓርቲው አብላጫ ድምፅ እንድያገኝ ለአባሉና ደጋፊው ጥሪ አቅርበዋል ።
የሸካ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ አበበ ማሞ እንደተናገሩት ብልፅግና በኢትዮጵያ ታርክ ውስጥ ሪፎርም በማድረግ የመጣና ትላንትን በማከም ህብረ ብሔራዊ አንድነት ለማፀናት እየሰራ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል።
ፓርቲው የማህበረሰብ የረጅም ጊዜ ጥያቄ የሆነው በክልል የመደራጀት መብት የመለሰና ፍታሀዊነትን ለማስፈን ቴፒን የብዘሀ ማዕከል ከተሞች አንዷ እንድትሆን ተደርጓል ነው ያሉት።
ዞኑ ከፍተኛ የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገቢያ የሚያቀርብ መሆኑን ገልፀው በዚህም የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሴርትፍኬሽን ማዕከል ወደ ስራ እንድገባ መደረጉን ተናግረዋል ።
በማህበራዊው ዘርፍ በጤናው መስክ ይስተዋሉ የነበረውን የሆስፒታል እጥረት ለመፍታት ግንባታዎች ተከናውኗልም ብለዋል
More Stories
አሜሪካ ለዩክሬን የ108 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ወታደራዊ መሳሪያ ሽያጭ ልትፈጽም ነው
ኢራን የቻይናው ፕሬዚዳንት ያቀረቡትን ባለ አራት ነጥብ የሰላም የውሳኔ ሐሳብ እንደምትደግፍ ገለጸች
የኢትዮጵያ እና የተመድ የ80 ዓመታት ታሪካዊ ቁርኝት