አርሰናል በ34ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ነገ በሜዳው ከኒውካስትል በሚያርገው ጨዋታ ጉዳት ላይ የነበረው ቡካዮ ሳካ እንደሚደርስ ሚኬል አርቴታ ተናግሯል፡፡
የእንግሊዛዊው ተጫዋች መመለስ ለቡድኑ ወደ አሸናፊነት መመለስ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ስፔናዊው ሰው ገልጿል፡፡
በተመሳሳይ ዩሪየን ቲምበርም ወደ ቡድኑ የተመለሰ ተጫዋች ሲሆን ሪካርዶ ካላፊዮሪም ለጨዋታው ዝግጁ መሆኑን አሰልጣኙ ተናግሯል፡፡
ባለፉት ሁለት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች የተሸነፉት መድፈኞቹ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚያደርጉት ጨዋታ ምሽት 1 ሰዓት ከ 30 ላይ በኤምሬትስ የሚጀመር ይሆናል፡፡
More Stories
አርሰናል 5 ተጨዋቾችን ያስመረጠበት የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ 11 ይፋ ተደረገ
ብሩኖ ፈርናንዴዝ የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን አሸነፈ
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ማጣሪያ ቅድመ ዝግጅቱን ዛሬ ይጀምራል