April 21, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በክልሉ በኢኮኖሚ ፤በመሰረተ ልማት፤በማህበራዊና አስተዳደር ዘርፍ በባለፉት 9 ወራት አዳጊ የሆነ ለዉጥ ተመዝግቧል ፦ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)

‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የፓርቲና የመንግሥት የ9 ወራት የስራ ግምገማ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል ። መድረኩ ማጠቃለያ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) የየዘርፉ አፈፃፀም ከባለፉት አመታት አንፃር አዳጊ የሆነ ለዉጥ ማሳየቱን ተናግረዋል። በክልሉ በኢኮኖሚ ፤በመሰረተ ልማት፤በማህበራዊና አስተዳደር ዘርፍ በባለፉት 9 ወራት የተሻሉ ተግባራት መከናወናቸዉን ገልፀዋል። የፓርቲ ስራዎችና የተለያዩ ኢንሼቲቮችን ተግባራዊ በማድረግ በክልል አመራር ድጋፍና ክትትል የተሰሩት ስራዎች አበራታች መሆናቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል ። የፓርቲ አመራርና አባላትን በአግባቡ በመገምገም ተልዕኮ የሚወጣ አባል በታችኛው መዋቅር መፍጠር ይገባልም ብለዋል። የመሄር ዝግጅት ስራን በተደራጀ አኳኋን ማስቀጠል፤የአረንጓዴ አሻራ ስራ፤የአከባቢ ጥበቃ ችግኝ ዝግጅት፤የሌማት ትሩፋት ፤ማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ በአግባቡ መሰብሰብና መሰል ስራዎች ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መሆናቸዉን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል ። የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን በበኩላቸዉ ፥ፖርቲና መንግሥት በመራቸዉ ስራዎች በዉጤት የሚዳሰስ ለዉጦች በባለፉት 9 ወራት ተመዝግቧል ብለዋል። በባለፉት ግዜያት አመራሩን የማጥራትና የመመዘን ስራ በመሰራቱ ክልሉ አዳጊ የሆነ ለዉጥ እየተመዘገበ እንደሚገኝ ተናግረዋል ። አመራሩ ተደራራቢ ተግባራትን እንዲሰሩ በተቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት የተሻለ ስራ መሰራቱን ገልፀዉ ተግባራትን አማጦ ከመፈፀም አንፃር ያሉ መሰረታዊ ጉድለቶችን በቀጣይ ማረም ይገባል ብለዋል። ለዚህም የድጋፍና ክትትል ስራዎችን እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ አጠናክሮ ማስቀጠል ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል ። የክልሉ ገቢ ለማሳደግ በ9 ወራት የተሰሩ የተሻሉ እንደሆኑ የተናገሩት አቶ ፍቅሬ አማን በቀሩት ወራት የዓመቱን ዕቅድ ለማሳካት የተለየ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል ። የክልሉ አጠቃላይ ስራዎች ስኬት የሁሉንም ርብርብ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል ።