በክልሉ የተከናውኑ የፓርቲ እና መንግስት ያለፉት ዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እንደቀጠለ ነዉ።
በመድረኩ ያለፉት ዘጠኝ ወራት አጠቃላይ የመንግስትን የስራ ሪፓርት ያቀረቡት የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ በማህበራዊ ዘርፍ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋጡ የልማት ስራዎች መሰራታቸዉን ተናግረዋል ።
የትምህርት ለትዉልድ ንቅናቄ በባለፉት 9ወራት 484 ሚልዮን ድጋፍ መገኘቱን ተናግረዉ ፥የትምህርት ቤት የዉስጥ ገቢ ለማሳደግ 263 ሚልዮን ብር መገኘቱን ገልጸዋል ።
ሞደል ቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ለማስፋፋት በተሰራው ስራ በክልሉ 30 ሞዴል ቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መገንባቱን ወ/ሮ ወሰነች በሪፖርታቸዉ አመላክተዋል ።
የትምህርት ግብአቶችን በተገቢዉ መንገድ ተደራሽ ለማድረግ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር የመጽሐፍ ጥምርታ 1ለ3 እንዲደርስ መደረጉን ገልጸዉ ለዚህም 130ሺህ መጽሐፍትን ኮፒ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል ።
በትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም 75ሺህ 838 ተማርዎች ተደራሽ ማድረግ መቻሉን የገለጹት የቢሮ ኃላፊዋ አጠቃላይ የትምህርት ተደራሽነት 806,720 ተማርዎች 1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትምህርት እየተከታተሉ ይገኛሉ ብለዋል።
የጤና ልማት ስራን በሚመለከት 471ሺህ የቤተሰብ የእናቶችና ህፃናት ጤና አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀው በዚህም 57ሺህ እናቶች በሰለጠነ ባለሙያ አገልግሎት ማግኘታቸውን ተናግረዋል ።
ማህበረተሰብ አቀፍ የጤና አገለግሎት የአባላት ምጣኔ በማሳደግ 48ሺህ 174 አዳዲስ አባላት ማፍራት መቻሉን ገልፀዉ ከአባላቱ 471 ሚልዮን ብር መሰብሰቡን ገልፀዋል።
የማህበረተሰብ ጤና መድሀኒት ቤት ቁጥር 22 ማድረስ መቻሉ በርፖርቱ የተመላከተ ሲሆን በለላ በኩልም በወባ በሽታ የሚከሰተው የሞት ምጣኔ ከነበረበት 15 በመቶ ወደ 7 በመቶ መቀነስ መቻሉ ተገልጿል ።
በባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ዘርፍ ዘርፍም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከሀገር ውስጥ ጎብኝዎች ባለፉት 1.14 ሚሊየን ብር በላይ የቱሪዝም ገቢ የተገኘ ሲሆን 3 ሀገር በቀል እውቀቶችን በመለየት ጥቅም ላይ እንዲውሉ የማድረግ ስራም ተሰርቷል።
ቋንቋን ለማሳደግ በተሰራው ጥረት በክልሉ ውስጥ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸው የነበሩ የናይ፣ የፃራ እና የዝልማሞ ቋንቋዎች መልሰው እንዲያገግሙ የማድረግ ስራ በውጤታማነት ተሰርቷል።
በሴቶች፣ ህጻናት እና ማህበራዊ ዘርፍ የሴቶች ተሳትፎና ውክልናን በማሳደግ 20 ሺህ ለአመራር ብቁ የሆኑ ሴቶችን ፑል የመለየት ስራ በመስራት ከዚህም ውስጥ 49 ሴቶች ወደ አመራርነት የማምጣት ተግባር መከናወኑ ተገልጿል።
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።