ልማት ማህበሩ የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ በሰንበት ገበያ የተለያዩ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለነዋሪዎች አቅርበዋል ።
ገቢያን ከማረጋጋት አንጻር የሰንበት ገበያ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የተናገሩት ሸማቾች ልማት ማህበሩ ለበዓል የሚሆን ምርት በማቅረቡ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል ።
ማህበሩ እያቀረበ የሚገኘውን የምርት ዋጋ ያነጻጸሩት ሸማቹቾች ቀይ ሽንኩርት ገቢያ ላይ ከ1መቶ 50 እስከ 1መቶ 60ሲሆን በልማት ማህበሩ የሰንበት ገቢያ 1መቶ 10፤ ዘይት ፈሳሽ ባለ 5 ሊትር በሱቅ 2ሺህ 5መቶና ከዚያ በላይ ስሸጥ በልማት ማህበሩ 2ሺህ 2መቶ ብር እየሸመቱ መሆኑን ተናግረዋል።
ልማት ማህበሩ የጀመረውን በጎ ተግባር በሌሎችም ምርቶች ላይ አሰፍተው እንድቀጥል የገለጹት ሸማቾቹ ህብረተሰብ ከልማት ማህበሩ ጎን በቁርጠኝነት በመቆም የልማት ስራዎችን እንደሚያፋጥኑ ጠቁመዋል።
የሸካ ልማት ማህበር የፋስካ በዓል ምክንያት በማድረግ ለሸማቹ ህብረተሰብ ካቀረበው ምርቶች መካከል ቀይ ሽንኩርት፣ ዘይትና ዱቤ ዱቄት ይገኙበታል።
የሸካ ህዝቦች ልማት ማህበር የጀመረው የሰንበት ገቢያ በበዓል ወቅት ከሚፈጠረው የዋጋ ንረት ታድጎናል ሲሉ የሸካ ዞን ማሻ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
More Stories
በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ የአቮካዶ ምርቶች ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ገበያ ተፈላጊ እያደረጓት ነው
ከወጪ ንግድ 607 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ
በጅማ ዞን የተመረተ ከ6.7 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ የአቮካዶ እና የሙዝ ምርት ለገበያ ቀረበ