የሩሲያ መንግስት በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ጦርነት ሳቢያ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ የሚታየውን የዋጋ መለዋወጥ ለመቋቋም ከመጋቢት 23 ቀን 2018 ጀምሮ የቤንዚን የውጭ ኤክስፖርት ለማገድ መወሰኑ ታውቋል።
የሀገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ኖቫክ የኢነርጂ ሚኒስቴር እገዳውን የሚጥል ረቂቅ ውሳኔ እንዲያዘጋጅ ትዕዛዝ የሰጡ ሲሆን እገዳው እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2018 ድረስ እንደሚቆይ የሩሲያ መንግስታዊ የዜና ወኪል ታስ ዘግቧል።
ሩሲያ ይህን እርምጃ የወሰደችው የሀገር ውስጥ የነዳጅ አቅርቦትን ለማረጋጋትና የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ነው ተብሏል።
ሩሲያ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ወደ 5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የሚጠጋ ቤንዚን ወደ ውጭ ሀገራት ልካለች። አሁን የተጣለው እገዳ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ የራሱ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ይገመታል።
መረጃው የ’ዘ ኢኮኖሚክ ታይምስ’ ነው።
More Stories
የነገ ትውልድ ተስፋ አረንጓዴ ልማትና ቱሪዝም
ህገ ወጥ የቡና ግብይት ቁጥጥርን ማጠናከር እንደሚገባ የካፋ ዞን ምክር ቤት አሳሰበ ።
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ