
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ልብስ ለብሰው ግን ደግሞ ሆዳቸው ባዶ የሆኑ አቅም ያጠራቸውን ወገኖቻችን በየአካባቢያችን ልናስባቸው ይገባል ሲሉ ተናገሩ፡፡የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ቁጥር 4 በመገኘትለአቅመ ደካሞች ማዕድ አጋርተዋል፡፡ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ÷ መሰል ተግባር በምናምነው ሃይማኖት፣ በመንፈሳዊ እና በዓለማዊውም የሚደገፍ ተግባር መሆኑን ጠቅሰው አቅም ካጠራቸው ጋር ያለንን ማካፈል ከተረፈው ብቻ ሳይሆን ካለው የሚደረግ ተግባር እንደሆነም አንስተዋል።ይህንን የመሰለውን ለአቅመ ደካሞች ማዕድ የማጋርት በጎ ተግባር እየደገፉ ያሉ ተቋማት እና አካላት ሊመሰገኑ እንደሚገባ ደግሞ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።
FBC
More Stories
ሮቦቶችም ተማሪ ሆኑ! በቻይና የተከፈተው የዓለማችን መጀመሪያው የሮቦቶች ትምህርት ቤት አስገራሚ እውነታ
የግል ጄታቸውን ለሕዝብ አምቡላንስ አገልግሎት የለገሱት ጋናዊው ቱጃር
ፌራሪ የመጀመሪያውን ባለ 5 መቀመጫ የኤሌክትሪክ መኪና አስተዋወቀ