March 29, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢራን የፓኪስታን ሰንደቅ ዓላማ የያዙ 20 ተጨማሪ መርከቦች በሆርሙዝ ሰርጥ እንዲያልፉ ፈቀደች

ኢራን የፓኪስታን ሰንደቅ ዓላማ የያዙ 20 ተጨማሪ መርከቦች በሆርሙዝ ሰርጥ እንዲያልፉ ፈ


ኢራን በፓኪስታን ስም የተመዘገቡ 20 ተጨማሪ መርከቦች ለሳምንታት ተዘግቶ በቆየው የሆርሙዝ ሰርጥ በኩል እንዲያልፉ መስማማቷን ፓኪስታን አረጋገጠች።

የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሻቅ ዳር ይህንኑ ውሳኔ በ‘ኤክስ’ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ያረጋገጡ ሲሆን፣ “እርምጃው የሚደነቅ እና ገንቢ ነው” ብለዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም “ይህ የኢራን እርምጃ የሰላም አብሳሪ እና በቀጣናው መረጋጋትን ለማምጣት የሚረዳ ነው፤ ውይይት፣ ዲፕሎማሲ እና መሰል መተማመንን የሚፈጥሩ እርምጃዎች ለጦርነት ብቸኛ መፍትሔዎች ናቸው” ብለዋል።

ፓኪስታን በመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት ዙሪያ ዛሬ (እሑድ) የሚካሄደውን የአራትዮሽ ስብሰባ ለማስተናግድ መርሐ-ግብር ይዛለች።

በአሜሪካ-እስራኤል እና በኢራን መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት አንድ ወር በደፈነበት በዚህ ወቅት፣ የቱርክ፣ የፓኪስታን፣ የግብፅ እና የሳዑዲ ዓረቢያ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በኢስላማባድ በመገኘት፣ ውጥረቱን ለማርገብ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ይመክራሉ።

የሆርሙዝ ሰርጥ የዛሬ ወር ገደማ በተቀሰቀሰው የአሜሪካ-እስራኤል እና ኢራን ጦርነት ምክንያት ከፈረንጆቹ መጋቢት ወር መጀመሪያ አንሥቶ በተግባር ተዘግቶ ቆይቷል።

ግጭቱ ከመከሰቱ በፊት በቀን በአማካይ 138 መርከቦች በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል ያልፉ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ።