ኢድ አልፈጥር በዓል በስኬት እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮምሽነር ዶክተር ካሳ ለመላዉ ለእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1,447ኛ ለኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ብለዋል።
የኢድ አልፈጥር በዓል በመላው የክልሉ አካባቢዎች ሀይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ በፍቅር እና በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቆ ወደስራ መገባቱን ኮምሽነር ዶክተር ካሰ ገልፀዋል፡፡
ኮሚሽነር ዶክተር ካሳ አክለውም የኢድ ሶላት በሚከናወንባቸው መስጊዶች እና አደባባዮች ላይ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር እንዳይከሰት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በየደረጃው የሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች ፤የእስልምና መሪዎች፤ወጣቶች ጋር በመቀናጀት ስምሪት ወስደው ወደ ተግባር መገባቱንም አስታውቀዋል።
የእምነቱ ተከታዮች በአደባባይ ሰላት በሚሰግዱበት ወቅት መላዉ የእምነቱ ተከታዮች ለሰላምና ለአንድነት ቅድሚያ በመስጠት እንደቀደመዉ ጊዜ ማክበር እንደማኖርባቸዉ ገልፀዉ።
መላው የእምነቱ ተከታዩች ለሰላት በህብረት በሚንቀሳቀስበት ወቅት የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰት አስፈላጊዉን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸዉ ያሳሰቡት ኮሚሽነሩ መኖሪያ ቤቶች አከባቢ ስርቆት እንዳይፈፀም ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ኮሚሽነር ዶክተር ካሳ ለመላዉ እስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን በዓሉ የሰላም፤ የፍቅር፤ የመተሳሰብ፤ የአንድነት እንዲሆን በራሳቸዉና በመላዉ የፖሊስ አመራሮች እና አባላት ስም ከልብ እመኛለሁ ሲሉም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል ሲል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዘግቧል፡፡
More Stories
አሜሪካ ለኢራን ፍልሚያ ተጨማሪ 200 ቢሊዮን ዶላር ጠየቀች!
በሸካ ዞን የፓርቲና የልማት ስራዎች አፈጻጸም እየተገመገመ ነዉ
ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ለ1,447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ