በሸካ ዞን በሁሉም መዋቅሮች የፓርቲና የመንግስት ሥራዎች አፈጻጸም የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች አካላት በተገኙበት በቴፒ ከተማ እየተገመገመ ይገኛል።
የፓርቲና የመንግስት ኢንሼቲቮችን በበላይነት በመምራትና ውጤታማነታቸው ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ አመራሩ በባለቤትነት በመምራት የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንዲያስችል የጋራ መግባባት ላይ እንዲደረስ ያለመ የውይይት መድረክ እንደሆነም ተጠቁሟል።
በወረዳና በከተማ አስተዳደር የተደረጉ የአመራር ግምገማና ምዘና አፈጻጸም እየተገመገመ ይገኛል።
የአመራር ምዘናው ጠንካራ ተቋም በመገንባት የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚረዳና አሰራሮችን በመትከልና የፓርቲውን ተልዕኮዎች በብቃት በመፈጸም ውጤታማ አሰራር እንዲኖር ማስቻል ዓላማው እንደሆነም ተገልጿል።
በውይይቱ አመራሩ ለቀጣይ ተልእኮ ራሱን የሚያዘጋጅ እና ለህዝቡ የላቀ ተጠቃሚነት ተግባራትን የሚመራበት አቅጣጫም የሚቀመጥ ይሆናል።
በመድረኩ የክልል ደጋፊ አመራሮች፣የዞን ማዕከል አጠቃላይ አመራሮችና የወረዳ/ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት እየተሳተፉ ይገኛሉ ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።