የሸካ ዞን ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 5ኛ ዙር፣ 13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 24ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ሪፖርት ለምክር ቤቱ ቀርቧል ።
በጉባኤው ላይ የአስፈጻሚ አካላትን የ2018 ዓ.ም የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ በዞኑ ለጤና ስጋት ከሆኑ በሽታዎች መካከል የወባ በሽታ ወረርሽኝ አንዱ እንደሆነ ተመላክቷል ።
በዚህም በ2018 በጀት ዓ.ም 6ወራት ውስጥ 58ሺ 8መቶ 39 ሰዎች የወባ በሽታ ተገኝቶባቸው የህክምና አገልግሎት መሰጠት መቻሉን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ገልፀዋል ።
የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል ከጤና ሚናስቴር የቀረቡ 21 ሺ 8መቶ አጎበሮችን ለ9ሺ 99 አባወራዎች እና እማወራዎች ማሰራጨት መቻሉን ዋና አስተዳሪው ጠቁመዋል ።
በሽታውን ለመከላከል ክትባት የመስጠት እና የኬሚካል ርጭት ስራዎች በስፋት በመሰራታቸው የስርጭት መጠኑ እየቀነሰ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡም የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል።
የጤና መድህን ስራን በተመለከተ 34 ሺ 55 የመዐጤመ አባል አባወራ እና እማወራ ውስጥ 92 ሺ 65 አባላት በድግግሞሽ የህክምና አገልግሎት እንዳገኙ ተገልጿል ።
More Stories
ሮቦቶችም ተማሪ ሆኑ! በቻይና የተከፈተው የዓለማችን መጀመሪያው የሮቦቶች ትምህርት ቤት አስገራሚ እውነታ
የግል ጄታቸውን ለሕዝብ አምቡላንስ አገልግሎት የለገሱት ጋናዊው ቱጃር
ፌራሪ የመጀመሪያውን ባለ 5 መቀመጫ የኤሌክትሪክ መኪና አስተዋወቀ