ማሻ፤ መጋቢት 1/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በመጋቢት 17 እና 18/2018 በሚዘጋጀው 4ተኛው ኢንቨስት ኢን ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ፎረም ላይም የጣሊያን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትርን ጨምሮ የጣሊያን ባለሀብቶች በፎረሙ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ኮሚሽነር ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን በኢትዮጵያ ካሉትን የጣሊያን ሪፐብሊክ አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ ጋር በሁለቱ አገራት የኢንቨስትመንት ትብብር ላይ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን መክሯል፡፡
የጣሊያን አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ በበኩላቸው፤ ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የቆየ የትብብር ግንኙነት በኢንቨስትመንትና በንግድ ዘርፍ ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ በተለያዩ የኢኮኖሚ ሪፎርሞች በመተግበር ለዓለም አቀፍ ባለሀብቶች አመቺ የሆነ የኢንቨስትመንት ምህዳር እየፈጠረች በመሆኑ ከጣሊያን ኩባንያዎች ጋር ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር ለማጠናከር ኮሚሽኑ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።
የጣሊያን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ባሉ የኢንዱስትሪ፣ በግብርና፣ በሀይል እና የመሰረተ ልማት ዘርፎች ተሳትፎን ለማሳደግ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተገልጿል።
# (አራዳ ኤፍ ኤም)
More Stories
በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ የአቮካዶ ምርቶች ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ገበያ ተፈላጊ እያደረጓት ነው
ከወጪ ንግድ 607 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ
በጅማ ዞን የተመረተ ከ6.7 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ የአቮካዶ እና የሙዝ ምርት ለገበያ ቀረበ