ማሻ፤ የካቲት 17/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ሁለቱ የለንደን ከተማ ክለቦች ቼልሲ እና ዌስትሃም ዩናይትድ ከእንግሊዝ እግርኳስ ማህበር የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።
ክለቦቹ የገንዘብ ቅጣት የተጣለባቸው ብዛት ያላቸው ተጫዋቾች ሜዳ ውስጥ ለፀብ በመዳረጋቸው ነው።
ከሳምንታት በፊት ቼልሲ ከዌስሃም ዩናይትድ በተገናኙበት እና ቼልሲ ከ2ለ0 መመራት ተነስቶ 3ለ2 ባሸነፈበት ጨዋታ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ላይ የሁለቱ ክለቦች ተጫዋቾች ፀብ ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል።
ጉዳዩን ሲያጣራ የቆየው የእንግሊዝ እግርኳስ ማህበር ክለቦቹ ተጫዋቾቻቸውን መቆጣጠር ባለመቻላቸው የገንዘብ ቅጣት ጥሎባቸዋል።
በዚህም መሰረት የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ 325 ሺህ ፓውንድ ተቀጥቷል።
ዌስትሃም ዩናይትዶች ደግሞ የ300 ሺህ ፓውንድ የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።
More Stories
አርሰናል 5 ተጨዋቾችን ያስመረጠበት የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ 11 ይፋ ተደረገ
ብሩኖ ፈርናንዴዝ የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን አሸነፈ
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ማጣሪያ ቅድመ ዝግጅቱን ዛሬ ይጀምራል