ማሻ፤ የካቲት 12/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ከሜዳው ውጭ ከዎልቭስ ጋር ባደረገው ጨዋታ 2 ለ 2 አቻ ተለያይቷል።
የሊጉ መሪ አርሰናል በቡካዮ ሳካ እና ሂንካፒ ግቦች 2 ለ ዐ ሲመራ ቢቆይም፥ በሊጉ መጨረሻ ደረጃ ላይ ለሚገኘው ዎልቭስ ቡዪኖ እና ካላፊዮሪ (በራሱ ላይ) ባስቆጠሯቸው ግቦች ሁለቱ ቡድኖች ነጥብ ተጋርተዋል።
ውጤቱን ተከትሎ 27 ጨዋታዎችን ያደረገው አርሰናል በ58 ነጥብ ሊጉን ሲመራ፥ 26 ጨዋታዎችን ያደረገው ማንቼስተር ሲቲ በ5 ነጥብ ልዩነት ይከተላል።
More Stories
ኢትዮጵያዊ በዳምጠው ከበደ ተጨማሪ ሜዳሊያ አገኘች
ቴፒ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት
የኤሲሚላን የቀድሞ ተጫዋች ፍራንኮ ባሬዚ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ