ማሻ፤ የካቲት 8/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጠናቅቋል።
ጉባኤው የተካሄደው” ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሐሳብ ነው።
መሪዎቹ 48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ውይይት ባደረገባቸው አጀንዳዎች ላይ መክረዋል።
የውሃ ደህንነት እና የንጽህና አጠባበቅ፣ የአጀንዳ 2063 ትግበራን እና አህጉራዊ ትስስር፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት፣ የሰው ኃይል ልማት፣ ተቋማዊ እና የፋይናንስ ሪፎርሞች፣ ቀጣናዊ አጋርነት እና አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላት ሚና ከተመረከባቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ።
ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁን ኢዜአ ዘግቧል።
(ኤፍ ኤም ሲ)
More Stories
ሮቦቶችም ተማሪ ሆኑ! በቻይና የተከፈተው የዓለማችን መጀመሪያው የሮቦቶች ትምህርት ቤት አስገራሚ እውነታ
የግል ጄታቸውን ለሕዝብ አምቡላንስ አገልግሎት የለገሱት ጋናዊው ቱጃር
ፌራሪ የመጀመሪያውን ባለ 5 መቀመጫ የኤሌክትሪክ መኪና አስተዋወቀ