ማሻ፤ ጥር 11/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በክልሉ በስድስቱም ዞኖች የከተራና ጥምቀት በዓል ያለምን የፀጥታ ችግር እና የትራፊክ አደጋ ሳይከሰት በሠላም መጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮምሽነር እና የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮምሽነር አስናቀ አፍቴ ተናግረዋል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለከተራና ጥምቀት በዓል ከመንበራቸው ወጥተው የነበሩ 993 ታቦታት መካከል 783 ታቦታት በሰላም ወደ መንበራቸው መግባታቸውን እና ነገ የሚከበረው የቃና ዘገሊላ ጨምሮ ቀሪዎቹ ታቦታት በቀጣይ ሶስት ቀናት በክብር ወደ ማደሪያቸው የሚመለሱ መሆኑንም ምክትል ኮምሽነሩ አመልክቷል።
የጥምቀት በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ በየደረጃዉ የሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ወጣቶች እና ለመላዉ ለክልሉ ህዝብ ኮሚሽኑ ምስጋና አቅርቧል ሲል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዘግቧል
More Stories
ሮቦቶችም ተማሪ ሆኑ! በቻይና የተከፈተው የዓለማችን መጀመሪያው የሮቦቶች ትምህርት ቤት አስገራሚ እውነታ
የግል ጄታቸውን ለሕዝብ አምቡላንስ አገልግሎት የለገሱት ጋናዊው ቱጃር
ፌራሪ የመጀመሪያውን ባለ 5 መቀመጫ የኤሌክትሪክ መኪና አስተዋወቀ