February 4, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የሸካ ዞን የ2018 ዓ.ም ልዩ ልዩ ስፖርቶች

ማሻ፤ ጥር 09/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በማሻ ከተማ እየተካሄደ ባለው የሸካ ዞን የ2018 ዓ.ም ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻሚፒዮና፣የባህል ስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ውድድር ዛሬ በተደረገ እግር ኳስ ጨዋታ  አንድራቻ ወረዳ ማሻ ወረዳን 2ለ1 በሆነ ዉጤት አሸነፈ።

ዛሬ በተደረገ መርሃ ግብር በእግር ኳስ አንድራቻ ወረዳ ማሻ ወረዳን 2ለ1 በሆነ ውጤት ያሸነፈ ሲሆን ሌሎችም ውድድሮች ፍጻሜያቸውን እያገኙ ናቸው።

በዚህም ዋንጫ ካስገኙ የባህል ስፖርቶች መካከል በወንዶች ኮርቦ 1ኛ ደረጃ አንድራቻ ወረዳ ያሸነፈ ሲሆን 2ኛ ማሻ ወረዳ እንዳሁም የኪ ወረዳ 3ኛ ደረጃ  በመያዝ አጠናቋል።

በተመሳሳይ ኮርቦ በሴቶች የፍፃሜ ዉድድር 1ኛ አንድራቻ ወረዳ 2ኛ ቴፒ ከተማ 3ኛ ማሻ ወረዳ እንዲሁም ድብልቅ ኮርቦ አንድራቻ ወረዳ በበላይነት ሲያጠናቅቅ ቴፒ ከተማ 2ኛ በመሆን ፍፃሜ አግኝቷል።

ቡብ በወንዶች 1ኛ ማሻ ከተማ 2ኛ ማሻ ወረዳ ቴፒ ከተማ 3ኛ የወጡ ሲሆን በሴቶች 1ኛ አንድራቻ 2ኛ ማሻ ከተማ በመሆን አጠናቋል።

በወንዶች ሻይ ማሻ ከተማ በበላይነት ሲያጠናቅቅ አንድራቻ ወረዳ እና የኪ ወረዳ 2ኛ ና 3ኛ ወጥተዋል በሴቶች ሻይ ማሻ ከተማ 1ኛ  ሲሆን አንድራቻ ወረዳ 2ኛ እንዲሁም ማሻ ወረዳ 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል።

100 ሜትር በወንዶች ይስሀቅ አንደመ:ኡስማን ኃይሌ:አንተነህ መብራቴ ከቴፒ ተከታትለው በመግባት አሸናፊ ሆነዋል: 200 ሜትር ወንዶች ማሻ ወረዳ 1ኛ ሲወጣ 2ኛ እና 3ኛ አንድራቻ አሸንፏል።

በሴቶች 200ሜትር 1ኛ ማሻ ወረዳ ሲያሸንፍ 2ኛ እና 3ኛ ቴፒ ከቴማ አሸንፏል።

በወንዶች 5000 ሜትር  ተረፈ አለሙ እና መልካሙ አድነው ከማሻ ወረዳ 1ኛና 2ኛ በመሆን በበላይነት አጠናቀዋል።

ነገ በሚኖረው መርሐ ግብር  ከጠዋቱ 3:00 ቮሊ ቦል አንድራቻ ወረዳ ከማሻ ወረዳ ለዋንጫ የሚገናኙ ሲሆን  ከቀኑ 7:00  ለዋንጫ ለማለፍ ማሻ ከተማ ከማሻ ወረዳ ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ እንዲሁም 9:00 የኪ ወረዳ ከአንድራቻ ወረዳ ይገናኛሉ።