ማሻ፣ ጥር 06/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) በካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ቼልሲ ከ አርሰናል የሚያደርጉት የለንደን ደርቢ ይጠበቃል።
የከተማ ተቀናቃኞቹ አርሰናል እና ቼልሲ በካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በስታምፎርድ ብሪጅ ምሽት 5፡00 ላይ ያደርጋሉ።
በአዲስ አሰልጣኝ እየተመሩ ወደ ጨዋታው የሚገቡት ቼልሲዎች በሜዳቸው እና በደጋፊያቸው ፊት የከተማ ተቀናቃኛቸውን ይፋለማሉ።
እንዲሁም ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ ተጉዞ ባካሄዳቸው ያለፉት 6 ጨዋታዎች ምንም ዓይነት ሽንፈት ያላስተናገደው አርሰናል ከሰማያዊዎቹ ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል።
በዚህ ጨዋታ ላይ የቼልሲ የልብ ምት የሚባልለት ሞይሰስ ካይሴዶ፣ ሮሚዮ ላቪያ እና ሌቪ ኮልዊልን እንደማይሰለፉ የተረጋገጠ ሲሆን÷ ኮል ፓልመር፣ ሬስ ጄምስ እና ማሎ ጉስቶም የመሰለፍ እድላቸውም አጠራጣሪ ነው።
እንዲሁም በአርሰናል በኩል ወሳኝ የተከላካይ መስመር ተጫዋቾቹ ሪካርዶ ካላፊዮሪ፣ ፒዬሮ ሂንካፔ እና ሞስኴራ በጉዳት ምክንያት እንደማይሰለፉ ተረጋግጧል። የዊሊያም ሳሊባ እና ሊያንድሮ ትሮሳርድ የመሰለፍ ጉዳይም አልተረጋገጠም።
በትናንትናው ዕለት በተካሄደው የካራባኦ ካፕ የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ ኒውካስልን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በሴንት ጀምስ ፓርክ በተካሄደው ጨዋታ የማንቼስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች አዲሱ ፈራሚቸው አንትዋን ሴሜኒዮ እና ራያን ቼርኪ ከመረብ አሳርፈዋል።
More Stories
የሸካ ዞን የታዳጊ ወጣቶች የእግርኳስ ቡድን የ2018 ክልል አቀፍ ውድድር የዋንጫ አሸናፊ ሆነ።
5ተኛው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የባህል ስፖርቶች ውድድር፣ የባህል ፌስቲቫል እና የታዳጊ ወጣቶች ምዘና ውድድር የታለመውን ግብ ያሳካ መሆኑ ተገለጸ።
ባካሪ ሳኛ ኢትዮጵያ ገባ