ማሻ፣ ጥር 06/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) ሰው ሰራሽም ሆኑ የተፈጥሮ አደጋዎች ሲከሰቱ ምላሽ ለመስጠት የሚያግዙ ሀገር በቀል ረጂ ድርጅቶች ሊበራከቱ እና ሊጠናከሩ እንደሚገባ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ድጉማ ገለጹ።
ለዚህም የውስጥ አቅምን የማደራጀት ሥራ መጠናከር እንዳለበት ነው ሚኒስትር ዴኤታው የተናገሩት።
ሚኒስትር ዴኤታው ይህን ያሉት ቤዛ ፖስትሪቲ የልማት ድርጅት የተሰኘ ሀገር በቀል ረጂ ድርጅት 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ባከበረበት መድረክ ላይ ነው።
ከ25 ዓመታት በፊት በኮምቦልቻ በክለብ ደረጃ የተመሰረተው ቤዛ ፖስትሪቲ፣ አሁን ላይ ከበርካታ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በጋራ እየሰራ ይገኛል።
በተለይም በአማራ እና አፋር ክልሎች የኤች.አይ.ቪ ስርጭትን ለመግታት፣ በቲቢ ሕመም ሕክምና፣ የሴት ልጆች ግርዛትን መከላከል፣ የዓረብ ሀገር ተመላሾችን ማቋቋም ጨምሮ ለወጣቶች የሥራ ዕድልን መፍጠር ድርጅቱ ከሚሰራባቸው በርካታ የሰብዓዊ ድጋፎች ውስጥ ተጠቃሽ መሆናቸው በመድረኩ ተገልጿል።
በተለይም በመንግሥት ተደራሽ ባልሆኑ አካባቢዎች ለአደጋ ምላሽ መስጠት ላይ አተኩሮ እንደሚሰራም ተመላክቷል፡፡
ቤዛ ፖስትሪቲን ጨምሮ ሌሎች ሀገር በቀል ድረጅቶች ከመንግሥት ጋር በመተባበርር የሚያደርጉት የሀብት ማሰባሰብ እና ድጋፍ የማድረግ ሥራ ሊጠናከር እንደሚገባም በመድረኩ ተገልጿል።
ድርጅቱ በቀጣይም በተለያዩ ክልሎች የሚያደርጋቸው ሰብዓዊ ድጋፎች እንዲጠናከሩ የአጋር አካላት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑ ተነስቷል።
የሀገር ውስጥ ረጂ ድርጅቶች በሚጠናከሩበት ሁኔታ ላይ ያተኮረው ሲምፖዚየሙ በመካሄድ ላይ ነው።
በመድረኩ የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመን ጨምሮ በርካታ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
EBC
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች