ማሻ ፣ ጥር 6/2018 (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በአንድራቻ ወረዳ ገማድሮ በግሉ ዘርፍና በህብረተሰቡ ተሳትፎ እየተከናወነ ያለው የከተማ መሠረተ ልማት ስራ አበረታች መሆኑን ነዎሪዎቹ ገለጹ።
የግሉ ዘርፍ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ያለው አበርክተው ከፍተኛ መሆኑ የሚታወቅ ከመሆኑም በላይ ከተሰማሩበት ልማት ጎን ለጎን የአካባቢውን ህዝብ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፍ ተጠቃሚ ከማድረግ አኳያ የድርሻቸውን እየተወጡ ይገኛሉ።
በዚሁ መነሻ በሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ ገማድሮ ቀበሌ በ1992 ዓ ም የቡና ኢንቨስትመንት መሬት ተረክበው ወደ ልማት የገባው የኢትዮ አግሪ ሴፍቲ ገማድሮ ቡና ኘሮጀክት ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠርና በአካባቢው ልማት ላይ የራሱን አሻራ እያኖረ የሚገኝ ኘሮጀክት ነው።
የኘሮጀክቱ መግባትን ተከትለው ከየአካባቢው የሰዎች ፍልሰት በመበራከቱ የህዝቦች አሰፋፈር ከተማን በመፍጠሩ ለነዋሪዎች ሚቹና ጽዱ በማድረግ የመሠረተ ልማት የማሟላት ስራን ኘሮጀክቱ ትኩረት ሰጥቶ በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን የገማድሮ ከተማ ነዋሪ አቶ ከበደ አንገሎ ተናግረዋል።
ለከተማ ዕድገት ከግሉ ኘሮጀክት ጋር በመተባበር የጉልበትና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ረገድ የበኩላቸውን ሚና እየተወጣን እንገኛለን ያሉት ሌላኛው የከተማ ነዋሪ ወይዘሮ እህታለም መንገሻ ናቸው።
ነዋሪዎቹ በአስተያየታቸው የገማድሮ ቡና ኘሮጀክት ለከተማ ውስጥ ለውስጥ መንገድ ስራ እያደረጋ ያለው ቀና ትብብር ተጠናክሮ እንድቀጥልና ለከተማው መሟላት የሚገቡ መሠረተ ልማት እንድሟላ የባለድርሻ አካላት ትብብር ከተጠናከር እንደነዋሪ የሚጠበቅብንን ኃላፊነት እንደሚወጡ ገልጸዋል።
የገማድሮ ቀበሌ ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ ተወካይ አቶ አርጀፎ አንደሞ በበኩላቸው ከተማው ኘሮክቱ በአካባቢው መግባትን ተከትለው የተፈጠረና በ2012 ጀምረው የታዳጊ ማዘጋጃ ቤትነት ዕውቅና በማግኘት በኘሮጀክቱና በህብረተሰቡ ተሳትፎ በርካታ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረው ለሌሎች የሚያስፈልጉ ልማቶች ብሎ ህዝቡ የሚያሱ እንደ ባንክ ያሉትን አገልግሎቶች እንድቋቋሙ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውንና በአጠቃላይ ከተማዋ ተስፋ ሰጭ ዕድገት ላይ ትገኛለች ብለዋል
More Stories
ዜጎች በመልዕክት መላላኪያ አማራጮች በሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡-የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
በሸካ ዞን አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እና የህግ የበላይነትን ለማስከበር ያለመ ዞናዊ የፀጥታ ግብረ ኃይል የምክክር መድረክ በቴፒ ከተማ ተካሄደ
ክልላዊ የተቀናጀ የማኅበረሰብ አቀፍ ተፋሰስ ልማት ማብሰሪያ ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል።