ማሻ፣ ጥር 06/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) የገንዘብ ሚኒስቴር እና ዓለም ባንክ የከተማ ምርታማ ሴፍቲኔትና ስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክትን ለማስፈጸም የሚውል የ250 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰመሬታ ሰዋሰው እና የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ማርያም ሳሊም ፈርመውታል።
ይህ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ የኢትዮጵያ መንግሥት በከተማ የሚኖሩ አነስተኛ ገቢ ያላቸዉን የህብረተሰብ ክፍሎች የኑሮ ሁኔታን ለማሻሻል እንዲሁም ወጣቶችና ሴቶችን በሥራ ገበያው ውስጥ ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመረዉን ስራ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያግዝ መሆኑን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡
#AMN
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ