February 4, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የተጀማመሩ የልማትና የሠላም ግንባታ ስራዎችን ለማስቀጠል የፀጥታ ሀይሉ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ ።

ማሻ ፣ የጥር 6/2018 (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8)‌‌‎ ‌‎በሸካ ዞን የማሻ ከተማ አስተዳር ፖሊስ ፅ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ግምገማ አካሂደዋል ።

በሸካ ዞን የማሻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ፅ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በተገመገመበት ወቅት የከተማዋን ሠላም በማጠናከር የልማት ስራዎች ከደር እንድ ደርሱ እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል ።

በመድረኩ ላይ የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የማሻ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ረ/ኢንስፔክተር ብሩክ ታደሰ በተለያዩ ዘርፎች ውጤታማ ስራ መሰራታቸውን ጠቁመዋል ።

በመድረክ ላይ የተገኙት የማሻ ከተማ ሠላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መሰረት ደምበሎ ስራዎችን በቅንጂት ከመስራት አንፃር የተከናወኑ ተግባራት ጥሩ መሆናቸዉን አስረድተዉ የታዩ ክፍተቶችን ለማረም ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ብለዋል።

የዉይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የከተማ ሰላም ለማስጠበቅ ተቀናጅተው እየሰሩ መሆናቸውን ጠቁመው ይህን በማጠናከር ለከተማ ልማትና ሰላም የበኩላቸውን እንደሚወጢ ገልጸዋል ።

ኮማንደር አስረሳሽ ወ/ፃድቅና ኢንስፐክተር ግርማ ሾደኖ ህብረተሰቡ በሠላም ወጥተዉ መግባት እንድችል የፀጥታ ስራዎች በከተማዉ እየከናዉነ መሆኑን ጠቁመዉ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል ።

የማሻ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ረ/ኢንስፔክተር ብሩክ ታደሰ በበኩላቸዉ የከተማዋን ሠላም ለማስጠበቅ በተሰራው ጠንካራ ስራ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ጠቁመው አሁንም ጠንካራ ጎን በማስቀጠልና ድክመቶችን በማረም ሁሉም ተቀናጅተው በመስራት የከተማ ሰላምና ልማት ማፋጠን እንዳለበት ተናግረዋል