February 4, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በዋና ዋና የልማት ዘርፎች ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ።

ማሻ፣ ጥር 04/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የ2018 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት አፈጻጸም ዙሪያ ቢሮው መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የክልሉ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ በዋና ዋና የልማት ዘርፎች ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል።

አስቀድሞ የሕዝቡን የልማት ጥያቄና ፍላጎት መመለስ እንዲቻል አመራሩ ለወቅቱ በሚመጥን ቁመና መገኘት እንዳለበት የሚጠበቅ በመሆኑ መልሶ የማደራጀትና የማስተካከል ሥራዎች መሠራታቸውን ጠቁመዋል።

ይህም ተግባር አመራሩ የተሻለ የመፈጸምና የማስፈጸም ቁመና እንዲኖረው ቀጣይነት ባለው መልኩ የማከናወን ስለመሆኑ ነው የገለጹት።

በኢኮኖሚ ዘርፎች በተለይም በግብርናው ዘርፍ ክልሉ ያለውን ተጨባጭ የመልማት አቅም መሠረት ባደረገ መልኩ እየተሠራ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው በተለይም
በግብርና አዝዕርት ሰብሎች 20.3 ሚሊየን ኩንታል ሰብል በምርት ወቅቱ ተሰብስቧል ብለዋል።

በሌማት ትሩፋት ሥራ የዶሮ እርባታና የወተት ምርት አቅርቦት በየገመዘረው እያደገና እሰፋ መጥቷል ይህንንም ስታንዳርዳይዝ የማድረግ ሥራ ይሠራል ብለዋል።

በሌላ በኩል 13ሺ 1መቶ 83 ቶን የታጠበና ያልታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ መላኩንና ይህም የዕቅዱ 71 በመቶ መሆኑን በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ በክልሉ እስካሁን ባለው ለ24ሺ 2መቶ 10 ዜጎች ቋሚ ሥራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረው በክልሉ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ ቁጥር ወደ 1.9 ሚሊዬን የማድረስ ዕቅድ መያዙንና እስካሁንም ለ231ሺ ዜጎች መስጠት መቻሉን ተናግረዋል።

በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ በክልሉ  የንግድ እንቅስቃሴን ለማቀላጠፍና ነጻና ፍትሐዊ ግብይት ይፈጠር ዘንድም 33 ኬላዎችን የማንሳት ሥራ መሠራቱን የጠቆሙት ኃላፊው  በክልሉ ሕገ-ወጥ የነዳጅ ንግድን የመከላከሉ ሥራ በተጠናከረ መልኩ እየተሠራ ይገኛልም ብለዋል።

ከገቢ አሰባሰብ አንጻርም የዕቅዱ 80 በመቶ በላይ መከናወኑንና በላይ መከናወኑንና ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሰመነጻጸር ሲነጻጸር 44% ብልጫ ያለው ገቢ ተሰብስቧል ነው ያሉት።

መሠሰተ ልማትን በሚመለከትም በትራንስፖርትና መንገድ ልማት ዘርፍ በየከተሞች ግንባታቸው ተጀመሩ መናኸሪያዎችን ሠርቶ የማጠናቀቅ ተግባር እየተከናወነ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።

20 የውሃ ፕሮጄክቶች በክልሉ እየተከናወኑ ይገኛሉ ያሉት አቶ የሺዋስ የሁሉም አፈጻጸም 75 በመቶ መድረሱን ጭምር አብራርተዋል።

በነዚህና መሰል የልማት ተግባራት ላይ የሕብረተሰቡ ተሳትፎ እያደገ መምጣቱንና በተለያዩ መንገዶች ከ220 ሚሊየን ብር በላይ ከሕብረተሰብ ተሳትፎ ማሳካት  ተችሏል ብለዋል።

የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ሊያረጋግጡ የሚያስችሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን የማስፋፋት ሥራ እየተሠራ መሆኑንና በክልሉ የመስኖ ሽፋን እንዲጨምር በተሠራው ሥራ ውጤት ተመዝግቧል ነው ያሉት።

ከዚህ ቀደም ክልሉ ከወርቅ ማዕዲን እምብዛም ተጠቃሚ እንዳልነበርና አሁን ላይ በአፈጻጸም ወቅቱ 255.28 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መላክ ተችሏል ብለዋል።

በክልሉ  5.5 ኪ.ሜ የኮሪደር ልማት መሥራት መቻሉን ተናግረው ይህም ከተያወው 2.5 ኪ.ሜ ዕቅድ አንጻር አበረታች ተግባር መሆኑን አመላክተዋል።
ማህበራዊ ዘርፍ በክልሉ 61ሞዴል ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እየተገነቡ መሆኑንና ከነዚህም 26ቱ ተጠናቀው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል።

የተማሪዎች ምገባን በተመለከተም ክልሉ የተሻለ አፈጻጸም ላይ መሆኑን ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ባሁኑ ሠዓት 806 ሺ 720 ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ መሆናቸው ተመላክቷል።

በጤናው ዘርፍ በወባ የመያዝ ምጣኔ 29.5 በመቶ መቀነስ የተቻለ ሲሆን በወባ ምክንያት ተኝቶ የመታከም ምጣኔም በእጅጉ ቀንሷል።

በማህቀረሰብ አቀፍ ጤና አገልግሎት 325 ሚሊየን ገደማ  ገደማ መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን ሕገ-ወጥ መድሃኒት ቁጥጥርን በተመለከተም ሰፊ ተግባር እየተከናወነ መሆኑ ተመላክቷል።

የፍትህ ተደራሽነትን ለማስፋፋት በርካታ ሥራዎች በመሠራታቸው ባሁኑ ሠዓት ከምንም በላይ በክልሉ ተስፋ ሰጪ ሠላምና መረጋጋት መስፈኑ አንደኛው ውጤት መሆኑን ተናግረዋል ኃላፊው።

የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሚዛን ከተማ ላይ ሥራ በመጀመሩ እስካሁን በ35 ዘርፎች ከ9ሺ በላይ አገልግሎቶችን ሰጥቷል።

በአጠቃላይ በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት የተከናወኑ ተግባራትን ይበልጥ በማጠናከር ለቀጣይ የአመራር ቁርጠኝኘትን በማጠናከር  የበልግ ሥራ ላይ ወሳኝ ዝግጅት በማድረግና ውጤት ለማስመዝገብ የሚሠራ ስለመሆኑ፣ እንዲሁም የከተማና የገጠር ኮሪደር ሥራዎችን በመመፈለገው መንገድ የመፈጸም ግብ መያዙን አቶ የሺዋስ ተናግረዋል።

ለአደጋዎች ፈጣን ምላሽ መስጠት፣የብሔራዊ መታወቂያ ተደራሽነትን እቅድ ከግብ ማድረስ፣
የጤና መድህን ተጠቃሚን ማሳደግ፣ የገቢ አሰባሰብን ማቀላጠፍ እንዲሁም የተጀመሩ መሠረተ ልማቶችን መጨረስ ቀጣይ አቅጣጫዎች ስለመሆናቸው ኃላፊው በመግለጫቸው አስታውቀዋል