ማሻ፣ ጥር 04/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) ኢትዮጵያ የጉባ ብስራቶች ከሆኑት አንዱ የሆነውን የኒውኩሌር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ይፋ ማድረጓን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር በትብብር እየሰራች ትገኛለች፡፡
ይኸው የኢትዮጵያ እና ሩስያ የኒውኩሌር ፕሮጀክት ትብብር ለሀገራቱ ግንኙነት አዲስ ምዕራፍ መሆኑን በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኤቭግኒ ተርኪሂን ተናግረዋል፡፡
ትብብሩ የሀገራቱን ግንኙነት ያደሰ ለኢትዮጵያም ብልፅግናን የሚያፋጥን መሆኑንም ነው አምባሳደሩ የገለፁት፡፡
አምባሳደር ኤቭግኒ ተርኪሂን ከኢቲቪ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ለዓመታት የዘለቀው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ወሳኝ በሆነ እጣፋት ላይ እንደሚገኝ አመላክተው፤ ኢትዮጵያ የጀመረችው ይኸው የኒውክሌር ፕሮጀክት ግዙፍና ለሀገሪቱ መፃኢ እድል ትልቅ አበርክቶ ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የኒውኩሌር ኃይል ማመንጫ ስራ ውስብስብ እና ጥልቅ የሆኑ ሂደቶችን የሚያልፍ በመሆኑ ሀገራቱ ያደረጉት ስምምነት በተለይም ለኢትዮጵያ በርካታ ተግዳሮቶችን የሚያቀልላት እንደሚሆን አመላክተዋል፡፡
አክለውም የተጠናቀቁ እና የተጀመሩ በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያ ወደ ፊት የሚያሻግሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በኒውኩሌር የጦር መሣሪያ ይዞታዋ ከዓለም ቀዳሚ የሆነችው ሩሲያ ከ 5 ሺህ 400 በላይ የኒውኩሌር ሩር ያላት ስለመሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ፡
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ