February 4, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የቤንች ብሄር የዘመን መለወጫ እና የምስጋና በዓል የሆነው “ቢስት ባር” የመተሳስብ እና የመከባበር እሴት በስፋት የሚገለፅበት በዓል ነው

ማሻ፣ ጥር 03/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) የቤንች ብሄር ኢኮኖሚያዊ ሥርዓትና የቢስት ባር ፍልስፍናና ባህላዊ መሠረቶች በሚል ርዕስ በቤንች ብሄር የዘመን መለወጫ እና የምስጋና በዓል የሆነው የቢስት ባር ፓናል ውይይት መድረክ በሲዝ ከተማ አስተዳደር ተካሂዷል።

‎የዘንድሮው 3ኛው ዙር የቤንች ብሄር የዘመን መለወጫ እና የምስጋና በዓል የሆነው ቢስት ባር በተለያዩ ኩነቶች እየተከበረ ይገኛል ።

‎ጥር 2/2018 ዝም በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር በወጣቶች የመጀመሪያው ዙር የበዓል ዋዜማ አከባበር የጀመረው በዓሉ ጥር 3/2018 ዝም በሲዝ ከተማ አስተዳደር የቤንች ብሄር ኢኮኖሚያዊ ሥርዓትና የቢስት ባር ፍልስፍናና ባህላዊ መሠረቶች በሚል ርዕስ በቤንች ብሄር የዘመን መለወጫ እና የምስጋና በዓል የሆነው የቢስት ባር ፓናል ውይይት መድረክ በሲዝ ከተማ አስተዳደር ተካሂዷል።

‎በፓናል ውይይት መድረኩ ላይ ከፌደራል፣ከክልል፣ከዞንና ከተለያዩ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተገኙ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የብሄሩ ተወላጆች ተሣትፈዋል።

የፓናል ውይይት ቢስት ባር ለቤንች ህዝብ በባህላዊ መስክ ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ባሻገር ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፋይዳው የጎላ እንደሆነ ተዳሷል።

‎በውይይት መድረኩ ተሳታፊ ከነበሩት መካከል አቶ ካናንስ ታደሠ፣አቶ ፀጋዬ አትርሴ፣ አቶ አሸናፊ ንጉሴ እና ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ እንደተናገሩት የቤንች ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ እና የምስጋና በዓል የሆነው ቢስት ባር የመተሳስብ እና የመከባበር እሴት በስፋት የሚገለፅበት በዓል ነው ።

‎ይህ ባህል ይበልጥ እንዲዳብር እና ለቀጣይ ትውልድ ለማሸጋገር በጥናታዊ ጽሁፎች የተደገፉ ወይይቶችን በማካሄድ በተለይ ወጣቶች ስለባሀላቸው እንዲያውቁና እንዲገነዘቡ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

‎ በመሆኑም የፓናል ውይይት ቢስት ባር ሲከበር ጀምሮ በየአመቱ እየተካሄደ ይገኛል ብለው በዘንድሮው ቢስት ባር  በፓናል ውይይት ላይ ቢስት ባር በባህላዊ መስክ ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ባሻገር ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፋይዳው የጎላ እንደሆነ መዳሰሱን ተናግረዋል።

‎ቢስት ባር ከቤንች ብሄር  የዘመን መለወጫ እና ሠርተው ያደረሱትን ምርት ለታላላቆቻቸው በማስቀመስ ፈጣሪን የሚያመሰግኑበት፣ ምርታቸውን እንዲባርክ ፈጣሪን የሚለምኑበት ሥርዓት ያለው ባህል ነው ብለዋል።

‎#ቤ.ሸ.ቴ