February 4, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሞዛንቢክ ጋቦንን አሸነፈች

ማሻ፣ ታህሳስ 19/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ ሞዛንቦክ ጋቦንን 3 ለ 2 አሸንፋለች።

በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቀን 9፡30 ላይ በተደረገው ጨዋታ የሞዛንቢክን ግቦች ዲዮጎ ካሊላ፣ ጄኒ ካታሞ፣ ፋይሳል ባንጋል ሲያስቆጥሩ÷ ኦባሚያንግ እና ሙኬቱ ሙሳውንዳ የጋቦንን ግቦች አስቆጥረዋል።

የዛሬው መርሐ ግብር ጨዋታዎች ቀጥለው ሲካሄዱ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ኢኳቶሪያል ጊኒ ከሱዳን እንዲሁም ምሽት 2:30 ላይ አልጄሪያ ከቡርኪናፋሶ፤ ምሽት 5 ሰዓት ኮቲዲቯር ከካሜሩን ይገናኛሉ።