ማሻ፣ ታህሳስ 19/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋገሾ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ልዑክ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የክልል ቢሮ ግንባታ ያለበትን ደረጃ ምልከታ አደረገ።
የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎቹ በዞኑ ቴፒ ከተማ በግል ባለሀብቱ ኢንጅነር ታደሰ አድማሱ በዘመናዊ መልክ የሚተከል የቡና ማሳንም ጉብኝተዋል ።
የቡና ማሳው በተለያዩ ዓይነት ቴክኖሎጂዎች ተደግፎ የሚለማ ሲሆን አሠራሩም የቡና ጥራትን በማስጠበቅ ተወዳዳሪ የሆነውን ቡና ለዓለም ገቢያ በብዛት እንዲቀርብ የሚያስችል ነው ተብሏል ።
በጉብኝቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋገሾን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል ።
More Stories
ሮቦቶችም ተማሪ ሆኑ! በቻይና የተከፈተው የዓለማችን መጀመሪያው የሮቦቶች ትምህርት ቤት አስገራሚ እውነታ
የግል ጄታቸውን ለሕዝብ አምቡላንስ አገልግሎት የለገሱት ጋናዊው ቱጃር
ፌራሪ የመጀመሪያውን ባለ 5 መቀመጫ የኤሌክትሪክ መኪና አስተዋወቀ