ማሻ፣ ታህሳስ 17/2018 (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደቡብ ምዕራብ ሪጅን በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ከባለድርሻ አካላትና ከቁልፍ ደንበኞች ጋር ውጤታማ የምክክር መድረክ አከናውኗል።
ተሳታፊዎች ተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥ እንዲቆም፣ ያረጁ የእንጨት ምሶሶዎች በኮንክሪት እንዲቀየሩ፣ የሰብስቴሽን እጥረት እንዲፈታና የአገልግሎት ክፍያ እንዲቀነስ ጠይቀዋል።
የሪጅኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ገብሬ በሰጡት ምላሽ፤ የመስመር ዝርጋታና የኮንክሪት ፖል ጥያቄዎችን ለመፍታት ዕቅድ መያዙን ገልጸዋል። የኃይል ተደራሽነትን ለማስፋትም ከጊቢ የኃይል ማመንጫ ለማምጣት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
ውይይቱ የተቋሙን ተጠያቂነት ለማስፈንና የፕሮጀክቶችን ስኬት ለመጨመር ያለመ ሲሆን፤ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ደንበኞችም የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
ተቋሙ በተመጣጣኝ ዋጋ አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብና የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን ቁርጠኛ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጧል። ዘገባው የደ.ምዕ. ሚዲያ ኔትዎርክ ነው።
More Stories
ሮቦቶችም ተማሪ ሆኑ! በቻይና የተከፈተው የዓለማችን መጀመሪያው የሮቦቶች ትምህርት ቤት አስገራሚ እውነታ
የግል ጄታቸውን ለሕዝብ አምቡላንስ አገልግሎት የለገሱት ጋናዊው ቱጃር
ፌራሪ የመጀመሪያውን ባለ 5 መቀመጫ የኤሌክትሪክ መኪና አስተዋወቀ