‹‹ሉሲ የእንሰት ኢንተርፕራይዝ ››የእንሰት ውጤቶች ላይ እሴት በመጨመር ለገበያ ለማቅረብ በ2015 ዓ.ም የተቋቋመ ኢንተርፕራይዝ ነው።
ኢንተርፕራይዙ የእናቶችን ጉልበትና ጊዜ የሚቆጥቡ 40 የቆጮ መፋቂያ ማሽኖችን በተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ለሚገኙ ማህበራት ማከፋፈሉን የኢንተርፕራይዙ ፕሮዳክሽን ማናጀር ወ/ሪት የትምወርቅ ሠይፉ ይናገራሉ፡፡
ቆጮ በባህላዊ መንገድ እንዲብላላ መሬት ውስጥ ተቀብሮ ከ3-4 ወር ጊዜ መጠበቅ ግድ ይል ነበር፡፡ የኢንተርፕራይዙ አባላት ችግሩን ለመፍታት ያካሄዱት ጥናትና ምርምር ውጤት የሆነው እርሾ ቆጮ ንፅህናውን እንደጠበቀ በ 7 ቀናት ውስጥ በጥሩ ሁኔታ እንዲብላላለ ማድረግ መቻሉንም ያስረዳሉ፡፡
ቆጮን በባህላዊ መንገድ ለምግብነት ማዋል ብቻ ሳይሆን እሴት ተጨምሮበትና ተቀነባብሮ ዱቄት፣ ኬክ፣ ኩኪስና ዳቦ ሊሆን መቻሉን አብራርተዋል።
የገበያና ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል ያሉት ወ/ሪት የትምወርቅ ቆጮን ኬክና ኩኪስ አድርገን ከአገር ውስጥ ገበያ አልፈን ወደ ባህር ማዶ መላክ ጀምረናል ብለዋል።
‹‹እሴት ሰንሰለትን መሠረት ያደረገ የሥራ ዕድል ፈጠራ›› የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሰፋፊ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የቀረፀው አዲሱ የዘርፉ እሳቤ አንዱ የትኩረት መስክ ነው፡፡
በዚሁ መሰረት ሚኒስቴር መ/ቤቱ የዕሴት ሰንሰለትን በጥናት በመለየት በየደረጃው ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል መመሪያ አዘጋጅቶ ወደ ሥራ አስገብቷል፡፡
More Stories
በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ የአቮካዶ ምርቶች ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ገበያ ተፈላጊ እያደረጓት ነው
ከወጪ ንግድ 607 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ
በጅማ ዞን የተመረተ ከ6.7 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ የአቮካዶ እና የሙዝ ምርት ለገበያ ቀረበ