አባላቱ በዓመት 150 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የታጠበና ደረጃ አንድ ቡናን ለዓለም ገቢያ በማቅረብ ተጠቃሚ ከመሆናቸውም በላይ በአካባቢው ገጽታ ላይ የጎላ ሚና መጫወታቸውን አመላክተዋል።
የተፈጥሮ ደንን በመጠበቅ በውስጡ የሚያመርቱትን ቡና በማህበር በመደራጀት በልፋታቸው ልክ ትርፋማ ለመሆን በዓመት 150 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የታጠበና ደረጃ አንድ ቡና ለዓለም ገቢያ ማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ አቻሜ ጌቱ ገልጸዋል።
በመጀመሪያ 18 አባላት የተቋቋመው ማህበሩ በአሁኑ ጊዜ የአባላቱ ቁጥር 37 መድረሱን የሚያስታውሱት የማህበሩ አባል አቶ አስቻለው ካቻ ከዚህ ቀደም የቡና ዋጋም ዝቅተኛ ከመሆኑም በላይ ከሌሎች አካላት የሚደርስባቸውን ተጽዕኖን ተቋቁመው አሁን ለደረሱበት ደረጃ መድረሳቸውን ተናግረዋል።
ባሁኑ ሠዓት የገበያ ትስስር ችግር መኖሩን የሚያነሱት አምራችና አቅራቢ አርሶ አደሮቹ መንግስት የበኩሉን ሚና እንድጫወት በመግለጽ በዩኒዬኑ በኩል ያለው የትርፍ ክፍፍል መዘገየትና የተለያዩ ድጋፍ ያለማድረግ ክፍተት እንዲቀረፍልን ሲሉ ጠይቀዋል።
በራሳቸው ማሳ ባመረቱትና በሚሰበስቡት ቡና መነሻ በማህበር ተደራጅተውበቴክኖሎጂ በማስደግፍ እሴት ጨምሮ ማዕከላዊ ገቢያ በማቅረብ ሂደት ጥራቱ ላይ ማህበሩ የማይደራደርና ምርታቸው በየዓመቱ ጥሩ ደረጃን በመያዝ ተፈላጊነቱና የአካባቢን ስም በማስጠራት በኩል ድርሻው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።
በማህበሩ ስራ ዕድል ከተፈጠረላቸው በርካታ ሰዎች መካከል አቶ ግርማ ግዛዎ ወደዚህ ስራ ከገቡበት ጊዜ አንስቶ በብዙ መንገድ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው ማህበሩ ዕድገት ትኩረት ሰጥቶ እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የቴፒ ገበሬዎች ቡና ህብረት ስራ ዩኒዬኑ ስራ አስ ኪያጅ አቶ ሰለሞን ጥላሁን አርሶ አደሮችን ዓለም ገቢያ እንድሳተፉ ለማድረግ በተሰራው ስራ 8 ማህበራትን ቀጥታ በማገናኘት የቡና ጥራቱን ለማስጠበቅ የቡና መፈልፈያ ማሽን ድጋፍና መሰል ተግባራትን እያከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ማህበራቱ የሚያነሱትን የትርፍ ክፍፍል መዘገየትን በሚመለከት ገንዘቡ ኦዲት ተደርገው ብድር የወሰዱት ካለመመለሳቸው ጋር ተያይዘው መስጠት አልቻልንም የሚሉት ስራ አስኪያጁ ትርፍና ኪሳራ ለይተን በጠቅላላ ጉባኤ ለማስወሰን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።
በማህበር ተደራጅተው ቡናን አጥበውና እሴት ጨምረው ለማዕከላዊ ገቢያ በመላክ ተጠቃሚ መሆናቸውን በሸካ ዞን የአንድራቻ ወረዳ ዮኪ ጭጭ የቡና አቅራቢና አምራች አርሶ አደሮች ተናገሩ።
More Stories
ግብርናን ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር የፋይናንስ ብድር አገልግሎት
በሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ እየተከናወኑ የሚገኙ የተቀናጁ የልማት ሥራዎች በክልልና በዞን ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ምልከታ ተደረገ
ቆጮን ኬክና ኩኪስ አድርገን ባህር ማዶ አሻግረናል – ሉሲ የእንሰት ኢንተርፕራይዝ