ማሻ ፣ የሰኔ 25፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ኢትዮጵያ እየተጠናቀቀ ባለው የበጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ቶን በላይ የቡና ምርት ማግኘቷን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል።
ባለስልጣኑ ሕገ-ወጥ የቡና ንግድን መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከፌዴራልና ከክልሎች የፀጥታ፣ ከግብርናና ንግድ ዘርፎች ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፤ የቡና ምርትን ከማሳደግ አንፃር በርካታ ስራዎችን እየተሰሩ በመሆኑ ውጤት ተገኝቷል።
በተጨማሪም ወደ ውጭ የሚላከውን የቡና ጥራት ይበልጥ ለማስጠበቅ ተጨማሪ አራት የቅምሻ ማዕከላት ለመክፈት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።
በዚህም የቡና ምርት በጥራትም ሆነ በብዛት በተሻለ ደረጃ ማደጉን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
የተገኘውን ስኬት ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል ሕገ-ወጥ የቡና ንግድና ዝውውር መግታት ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ማለታቸውን የኢትዮጵያ ሬዲዮ ዘግቧል።
ባለፉት 11 ወራት 409 ሺህ ቶን ቡና ለውጭ ገበያ መቅረቡ የሚታወስ ነው።
ኢቢሲ
More Stories
በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ የአቮካዶ ምርቶች ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ገበያ ተፈላጊ እያደረጓት ነው
ከወጪ ንግድ 607 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ
በጅማ ዞን የተመረተ ከ6.7 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ የአቮካዶ እና የሙዝ ምርት ለገበያ ቀረበ