July 4, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ለሀገሪቱ ዋነኛ የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኝ ቡና እንደ ወረዳ ከ30 ሺህ ሄክታር በላይ ሽፋን መኖሩን በሸካ ዞን የየኪ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ።

ማሻ ፣ የሰኔ 26፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ‎‎የቡና ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ከ1ሺህ 2 መቶ ሄክታር ለመጎንደልና ለመንቀል ዕቅድ ተይዞ ወደ ስራ መግባቱ ተጠቅሷል።

‎የየኪ ወረዳ በቆ ቀበሌ አርሶ አደር ጀማል አባ ቡልጋና ኑረድን መሐመድ እንሚናገሩት ቡና ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ጊዜ ያለፈባቸውን ቡናን በመጎንደል ከወረዳ ግብርና ጋር በመሆን የተሻሻሉ ዝርያ ያላቸውን ቡና በክላስተር ተደራጅተን ወደ ስራ ገብተናል ይላሉ።

‎ሌሎች የዞኑ ወረዳዎችን ጎብኝተው ምርጥ ተሞክሮ በመቀመር ከግብርና ባለሙያዎች ጋር በመሆንና በኩታ ገጠም እርሻ ያረጁ ቡናዎችን በማስወገድ እንዲሁም በምርምር ማዕከሉ የተሻሻሉ ምርጥ ዘር በመትከል የአረም ስራን በጋራ በመስራታቸው በዘጠኝ ወር ውስጥ ከፍተኛ ውጤት ማየት መጀመራቸውን አርሶ አደሮቹ ገልጸዋል።

‎ የየኪ ወረዳ ግብርና ደን አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ጽህፈት ቤት የቡና ሻይ ቅመማቅመም ልማትና ጥበቃ ቡድን መሪ አቶ አሸብር አበበ ቡና በወረዳው ካለው የቡና ሽፋን ከግማሽ በላይ ምርታማነት የቀነሰና ያረጁ ቡና ከመሆናቸውም በላይ ቀደም ብሎ ምንጫቸውም ሆነ ምርታማነታቸው ሳይታወቅ የተተከሉ ቡናን ለመቀየርና ለማደስ

‎5 መቶ ሀረክታር በጉንደላ 8 መቶሀረክታርን በነቀላ በአጠቃላይ 1ሺህ 2መቶ ሄክታር ለማደስ ዕቅድ ከተያዘው እስከአሁን ባለው 3መቶ 35 ሺህ ሄክታር በመንቀል 1መቶ18 ነጥብ 75 ሄክታርን በኩታ ገጠም በማከናወንና የቴፒ ግብርና ምርምር ማዕከል በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች የቡና ኩታ ገጠም ስራን የተሻሻሉ ችግኞችን በማቅረብ ስልጠናና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል ሲሉ አቶ አሸብር ገልጸዋል።

‎የየኪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ተሰማ በበኩላቸው በቡናና ቅመማቅመም ዘርፍ ከፍተኛ አቅም መኖሩን ተናግረው የአርሶ አደሩን ምርትርትና ምርታማነት ከማሳደጉ ረገድ የምርምር ማዕከላት የሚያደርጉት ድጋፍ የተሻለ በመሆኑ አጠናክረን እናስቀጥላለን ብለዋል።

‎ካሳሁን ደንበሎ