በቀጣይ 90 ቀናት የተቀመጡ ዕቅዶችን በውጤታማነት በመፈጸም እመርታዊ ውጤት ለማስመዝገብ ርብርብ ማድረግ ይኖርብናል፦አቶ ፍቅሬ አማን
ማሻ ፣ የሰኔ 06፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ የቀጣይ 90 ቀናት የመንግስትና የፓርቲ ሥራዎች ንቅናቄ ዕቅድን በውጤታማነት ለመተግበር ውይይት ተካሂዷል።
በመድረኩ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ባለፉት ዓመታት በሁለንተናዊ የትብብር መስክ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተከናውነው በርካታ ውጤቶች ተመዝግበዋል።
በዚህም ካለፉት ሥራዎቻችን ልምድ በመቅሰም፣ ድክመቱን አርመንና ስኬቱን አስቀጥለን፣ ወደ ላቀው ምእራፍ ህዝብን እና ሀገርን ለማሸጋገር መሠረት የሚጥል አሻራ ለማኖር በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
በቀጣዮቹ 90 ቀናት በውጤታማ ቅንጅት በመመራት የየዕለቱን ተግባር በውጤት የሚለካ አፈጻጸም መኖር እንዳለበት ጠቅሰዋል።
በቀሪ 90 ቀናት የመኸር ግብርና በተሳካ መንገድ እንዲከናወን፣ ለዚህም አስፈላጊ የሆኑ የግብርና ግብዐቶች በጊዜ እንዲዳረሱ መሥራት፣ የከተማና የገጠር ኮሪደር ልማት ስራን ማፋጠን፣የአሬንጓደ አሻራ፣ የበጎ አድራጎት ሥራዎች፣ የሠላም እሴት ግንባታ ማፅናት እና ሌሎች ተግባራትነን 7/24 በመሰራት የተቀመጡ ግቦችን ማሳካት ይጠበቃል ።
በሌማት ትሩፋት የተጀመሩ እና ውጤት እያመጡ ያሉ ተግባራት ሰፍተውና ተጠናክረው እንዲቀጥል ብርቱ ትግል ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ፍቅሬ የተጀመሩ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እና ጥራት ደረጃ ልክ እንዲጠናቀቁ ሁለንተናዊ ሥራ መሠራት ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል።
የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት በታቀደላቸው መሠረት እንዲከናወኑ ሁላችንም በተባበረ ክንድ መፈጸም ያስፈልጋል ያሉት የንቅናቄ ሰነዱን ያቀረቡት የፓርቲው የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግርማ ባሻ ናቸው።
ክልል ኮሚኒኬሽን
More Stories
የአየር ጠባይ ትንበያ መረጃ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት በታቀደው መሠረት እንዲከናወን ድርሻውን ተውጥቷል – ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር)
መጪው የበጋ የአየር ጠባይ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሚኖርባቸው አካባቢዎች በደረሱ ሰብሎች ላይ ተጽዕኖ ሊያደርስ ይችላል ተባለ።
የወባ መከላከያ ክትባት በሽታውን ለማጥፋት በማለም ለተጀመረው ርብርብ ትልቅ እገዛ ያደርጋል አሉ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ።