ምክር ቤቶች የህዝቡ ሁለተናዊ ተጠቃሚነት እንድረጋጥ ድርሻቸው የጎላ በመሆኑ የድጋፍና ክትትል ስራዎችን ማጠናከር እንደምያስፈልግ ተጠቆመ ።
ማሻ ፣ የሰኔ 06፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የየኪ ወረዳ ምክር ቤት 5ኛ ዙር 12ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤን በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
በዚህ ጉባኤ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የየኪ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ መላኩ ብዙነህ በወቅቱ እንደገለፁት ምክር ቤቶች የወከላቸውን ህዝብ ሁለተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንድፈቱ በማድረግ በኩል ድርሻቸው የጎላ እንደሆነ ተናግረዋል ።
በመሆኑም የወረዳው ህዝብ በኢኮኖሚ ፣ ማህበራዊና በተለያዩ ዘርፎች ተጠቃሚ እንድሆኑ ለማስቻል በየደረጃው ካሉ ምክር ቤቶች ጋር በመሆን ስሰራ መቆየቱን ጠቁመው የአካባቢውን የገቢ አቅም ባገናዘበ መልኩ ገቢን አሟጦ መሰብሰብ ያስፈልጋል ስሉ ጠቁመዋል ።
የአስፈጻሚ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የ9ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳውት ተሰማ የቀረበ ሲሆን የባለፈውን ቃለ-ጉባኤን መርምሮ ማፅደቅን ጨምሮ አምስቱ የገጠር ቀበሌዎችን ወደ ከተማ መካለላቸውን መርምሮ ምክር ቤቱ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በዚህ ጉባኤ ላይ የየኪ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ መላኩ ብዙነህ ፣ምክትል አፌ ጉባኤ ወ/ሮ ድርጀት ከበደ፣ የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ አስቻለው አየለ
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።