ማሻ ፣ የሰኔ 06፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ኢትዮጵያ ስደተኞችን ተቀብላ በማስተናገድ እያከናወነች ያለው ተግባር እና ጥረት የሚደነቅ ነው አሉ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ።
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲን በብሔራዊ ቤተመንግስት ተቀብለው አነጋግረዋል።
ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ከውይይቱ በኋላ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በርካታ ስደተኞችን ተቀብላ በማስተናገድ ላይ ትገኛለች።
በአሁኑ ወቅትም ከደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን እና ከሌሎች ሀገራት ስደተኞችን እየተቀበለች መሆኑን አንስተዋል።
ኢትዮጵያ ስደተኞችን ተቀብላ በማስተናገድ እያከናወነች ያለው ተግባርና ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው፤ ለዚህም የሚደረገው ድጋፍ እንደሚጠናከር ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ከዚህ በተጨማሪ ስደተኞችን ከመቀበል እና ከማስተናገድ አንጻር የኢትዮጵያን መልካም ተግባር ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲያውቀውና ድጋፍ እንዲያደርግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እና የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ያደረጉት ውይይት ፍሬያማ እንደነበር ውይይቱን የተከታተሉት የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ጠይባ ሀሰን አስታውቀዋል።
በተለይ በኢትዮጵያ በሚገኙ ስደተኞች ዙሪያ እንዲሁም ለስደተኞች ድጋፍ በሚጠናከርበትና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል ብለዋል።
ፋና
More Stories
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።