ማሻ ፣ የሰኔ 02፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ዘንድሮ በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና መሰጠት መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
በ51 ዩኒቨርሲቲዎች በተዘጋጁ 87 የፈተና ማዕከላት ፈተናው እንደሚሰጥም ነው ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የተናገሩት፡፡
በዚህ ዓመት እየተሰጠ ባለው የመውጫ ፈተና 190 ሺህ 787 ቅድመ መደበኛ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ጠቅሰዋል፡፡
ከዚህም ውስጥ 102 ሺህ 360 ተማሪዎች ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
ፈተናው በ238 የትምህርት መርሐ ግብሮች በሁሉም የፈተና መስጫ ማዕከላት በበይነ መረብ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል፡፡
ፋና
More Stories
ዜጎች በመልዕክት መላላኪያ አማራጮች በሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡-የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
በሸካ ዞን አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እና የህግ የበላይነትን ለማስከበር ያለመ ዞናዊ የፀጥታ ግብረ ኃይል የምክክር መድረክ በቴፒ ከተማ ተካሄደ
ክልላዊ የተቀናጀ የማኅበረሰብ አቀፍ ተፋሰስ ልማት ማብሰሪያ ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል።