August 2, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

10 ደቂቃዎችን በመዘግየቷ የበርካቶችን ሕይወት ከቀጠፈው አደጋ የተረፈችው ህንዳዊት

ማሻ ፣ የሰኔ 06፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ‎‎ በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት በረራ ያመለጣት ህንዳዊት ለበርካቶች ህይወት መጥፋት ምክንያት ከሆነው አደጋ 10 ደቂቃዎችን በመዘግየቷ መትረፏን ኤንዲ ቲቪ ዘግቧል።

ከባለቤቷ ጋር በለንደን ከተማ የምትኖረውና ከአደጋው በኋላ ከኤንዲ ቲቪ ጋር ቃለምልልስ ያደረገችው ቦሆሚ ቻውሃን የእረፍት ጊዜዋን አህመዳባድ ከሚገኙ ቤተሰቦቿ ጋር አሳልፋ በበረራ ቁጥር 171 ለመብረር ትኬት ቆርጣ ነበር።

ሆኖም ወደ አውሮፕላን ማረፊያው እያመራች በነበረበት ወቅት ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳጋጠማት እና አስር ደቂቃ ዘግይታ አህመዳባድ አየር ማረፊያ ስትደርስ ግን ወደውስጥ እንዳትገባ በመከልከሏ መናደዷን ገልፃለች።

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላም እዛው አየር መንገዱ ውስጥ እያለች ወደለንደን ልትጓዝበት የነበረው አውሮፕላን መከስከሱን ማየቷን ተናግራለች።

ኢቢሲ