ማሻ ፣ የግንቦት 19፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) እ.ኤ.አ. በ2014 በዩክሬን ‘የዩሮማይዳን’ መፈንቅለ መንግስት መደረጉን ተከትሎ፤ በዶንባስ ህዝብ ላይ ሲደርሱ የነበሩ በደሎችን ለማስቀረት ሩሲያ በዩክሬን ወታደራዊ ዘመቻ ከመክፈት ውጭ ሌላ አማራጭ አልነበራትም ሲሉ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንቱ በክሬምሊን ከሀገሪቱ ባለሀብቶች ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ፤ ሞስኮ በአጎራባች ሀገራት ያሉ የሩሲያ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ችግር ችላ ማለት እንደማትችል ገልጸዋል።
ምዕራባውያን ዲሞክራሲ እንዲሰፍን እና ምርጫ መደረግ እንዳለበት ሁልጊዜ ቢሰብኩም፤ መፈንቅለ መንግስትና ደም አፋሳሽ ጦርነት እንዲፈጠር ምክንያት እየሆኑ መሆኑንም አንስተዋል።
ፑቲን የዩክሬን የሚንስክ ስምምነቶችን አለማክበር እና በሩሲያኛ ተናጋሪዎች መብት ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት የግጭቱ ዋና መንስኤ እንደሆነ በመጥቀስ፤ የኪየቭን ድርጊት “ዘር ማጥፋት” ሲሉም ገልጸውታል።
ዩክሬን ከኔቶ ጋር የመቀላቀል አዝማሚያዋን እንድታቆም እና ገለልተኛ ሀገር እንድትሆን እንዲሁም ክሬምያ እና ሌሎች አራት የቀድሞ የሩሲያ ግዛቶች ያሏቸውን አካባቢዎች የሩሲያ ስለመሆናቸው እውቅና እንድትሰጥ መጠየቃቸውን አርቲ ዘግቧል።
ኢቢሲ
More Stories
የአሜሪካ ወታደሮች ላይ የተሰነዘረውን የጥቃት ሙከራ ተከትሎ ዋሽንግተን ኢራን ላይ “ከፍተኛ” ጥቃት ፈጸመች
አሜሪካ በኢራን ጦርነት ከ37 ቢሊየን ዶላር በላይ እንዳወጣች ተገለፀ::
አሜሪካ የመርከቦችን እንቅስቃሴ እያወኩ ነው ባለቻቸው የኢራን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ አዲስ ጥቃት ፈጸመች፡፡