ማሻ ፣ የግንቦት 08፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) በሸካ ዞን ማሻ ወረዳ የ2017 ዓ/ም የበልግ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በማሻ ወረዳ ጋዳ ቀበሌ የማብሰሪያ ፕሮግራም ተካሄዷል ።
በማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የማሻ ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪና የመንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተግባሩ እዳሮ እንዳሉት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ጥምር ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ይተከላሉ ብለው እንክብካቤም በአግባቡ መደረግ እንዳለበት አንስተዋል።
የማሻ ወረዳ ግብርና ደን አከባቢ ጥበቃ ህብረት ስራ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ልሳኑ አለማየሁ በበኩላቸው በወረዳው በ2017 የበልግ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 3 መቶ 63 ሺህ 1መቶ 90 ለመትከል ዕቅድ መያዙን ገልፀው በጠቅላላ በ2017 ዓ/ም 3 ሚሊዮን 7መቶ 14 ሺህ 880 ችግኝ ለመትከል መታቀዱን ተናግረዋል ።
የተለያዩ ጠቀመታ ያላቸው 3 ሚሊዮን 922ሺህ ችግኝ መዘጋጀቱንም ገልፀዋል።
በመርሃ ግብሩ የወረዳው ምክትል ዋና አስተዳደርና የመንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ተግባሩ እዳሮ፤ የወረዳዉ የጽ/ቤት ሀላፊዎች፤ ባለሙያዎችና የአከባቢ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በልጃለም ማሞ
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ