ማሻ ፣ የግንቦት 10፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም)በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 34 ሺህ 258 ህጻናት የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
ክልሉ በማህበረሰቡ እገዛ የትምህርት ቤቶች ምገባ ዘንድሮ መጀመሩን የቢሮው ምክትል ኃላፊና የመማር ማስተማርና ምዘና ዘርፍ ኃላፊ ደስታ ገነሜ (ዶ/ር) ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።
በዚህም በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በአንደኛና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ልዩ ድጋፍ ለሚፈልጉ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።
በ278 ትምህርት ቤቶች 34 ሺህ 258 ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው÷ መርሐ ግብሩ ከማህበረሰቡ በዓይነትና በጥሬ ገንዘብ ሀብት በመሰብሰብ የሚፈጸም ነው ብለዋል።
በቀጣይም በልዩ ሁኔታ ማህበረሰቡን፣ ባለሃብቱን እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን በማሳተፍ የምገባ መርሐ ግብሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየተሰራ መሆኑን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።
More Stories
የአየር ጠባይ ትንበያ መረጃ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት በታቀደው መሠረት እንዲከናወን ድርሻውን ተውጥቷል – ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር)
መጪው የበጋ የአየር ጠባይ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሚኖርባቸው አካባቢዎች በደረሱ ሰብሎች ላይ ተጽዕኖ ሊያደርስ ይችላል ተባለ።
የወባ መከላከያ ክትባት በሽታውን ለማጥፋት በማለም ለተጀመረው ርብርብ ትልቅ እገዛ ያደርጋል አሉ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ።