ማሻ፣ ሚያዝያ 30፣ 2017 (ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በ80ኛው የሩሲያ የድል በዓል ለሚሳተፉ የሀገራት መሪዎች ማምሻውን በክሬምሊን ቤተ መንግስት በተካሄደው የአቀባበልና የእራት ግብዣ ስነ ስርዓት ላይ ተሳትፈዋል።
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በድል ቀን በዓል ላይ ለመሳተፍ ለመጡ የሀገራት መሪዎች አቀባበል አድርገዋል።
በስነ-ስርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ እና የሌሎች ሀገራት መሪዎች መሳተፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የድል በዓሉ 2ኛው የዓለም ጦርነት ማብቃቱን ተከትሎ በተለይም የቀድሞው ሶቪየት ኅብረት ጦር የተቀዳጀውን ድል በማሰብ በሞስኮ የቀይ አደባባይ የሚካሄደውን ከፍተኛ ወታደራዊ ትርኢት ጨምሮ ሌሎች መርሃ ግብሮች ይከናወናሉ።
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ