ማሻ ፣ የመጋቢት 24፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ትናንት ፤ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና በሚል መርህ ቃል ባለፋት የለውጥ አመታት በየዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን የሚገምግም እና የለውጡን ትሩፋቶች የሚዘክር መድረክ በቦንጋ ከተማ ተጀምሯል ።
የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪው መድረኩን ሲከፍቱ መጋቢት 24 ኢትዮጵያን የሚያሻግሩ መሰረቶች የተጣሉበት በመሆኑ ሁሌም ይዘከራል ብለዋል ።
ባለፉት የለውጥ አመታት የህዝቡን የጋራ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ተግባራት በየዘርፉ መከናወናቸውንም የመንግስት ዋና ተጠሪው አውስተዋል መላው አመራርና ህዝቡ የለውጡ ትሩፋቶችን ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የተጀመረውን ርብርብ እንዲያጠናክረው ጥሪ አቅርበዋል ።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር እና የብልፅግና ፓርቲ ስራአስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ማስረሻ በላቸው በበኩላቸው የለውጡ መንግስት በየዘርፉ የቀየሳቸው አቅጣጫዎች የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቁመዋል ።
ከተረጂነት ለመላቀቅ በተደረገው ርብርብ የግብርና ምርታማነት ማደጉን በመጥቀስ።
በሰላም፣ብዝሃነት እና አብሮነት ዕሴቶች ግንባታ ዘርፍ በተከናወኑ ተግባራት ወንድማማችነትንና ትብብርን የሚያስቀድም የፖለቲካ ስርዓት መገንባት መቻሉን አቶ ማስረሻ ጠቁመዋል ።
መጋቢት 24ን ማስታወስ ባለፉት 7 አመታት የተከናወኑ ተግባራትንና የተመዘገቡ ድሎችን ለማስቀጠል የሚያስችል መነሳሳት እንደሚፈጥር የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር እና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ማስረሻ በላቸው አስገንዝበዋል።
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።