ማሻ ፣ የመጋቢት 23፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የቴፒ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን በነባራዊ ሁኔታ ጥናት ግኝቶችና የከተማዋን ራዕይ ለመተለም ባለድርሻ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው የሕብረተሰብ ተወካዮች ጋር የውይይት መድረክ በቴፒ ከተማ ተካሄደ።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የቴፒ ከተማ ከንቲባ አቶ ወንድሙ ግርማ እንደገለጹት ከተማን በፕላን ለማስመራት የ13 ወራት የከተማ የፕላን ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮዽያ ህዝቦች ክልል የከተሞች ፕላን ኢንስቲቲዩት ከፍተኛ ፕላነርና የቴፒ መዋቅራዊ ፕላን ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ታከለ ጉበላ በበኩላቸው የከተማዋን መዋቅራዊ ፕላንና ራዕይ ለመተለም በሚደረገው ጥረት ውስጥ የማህበረሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተናግረዋል ።
የቴፒ ከተማ ነባራዊው የፕላን ሁኔታ ምን እንደሚመስል ያብራሩት አቶ ታከለ በከተሞች ሁለንተናዊ ዕድገት እንዲረጋገጥ ከተሞች በትክክለኛው ፕላን ሊመሩ እንደሚገባ አሳስበዋል ።
ቀደም ሲል በከተማዋ የተዘጋጀ ፕላን ውጤታማ እንዳልሆነ ተናግረው ቀጣይ ከተማዋን ለማዘመን ዕራይ አስቀምጦ መስራት እንደሚያሰፈልግም ገልጸዋል ።
የከተማዋን መዋቅራዊ ፕላንና ራዕይ ለመተለም በሚደረገው ጥረት ውስጥ የማህበረሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ እንደሆነም ተጠቁመዋል ።
በ2050 ቴፒ ከተማን ፅዱ፣ ለኑሮ ምቹ ፣ለቱሪዝም መዳረሻ
ማዕከል ተመራጭ ፣የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፣ የንግድ አገልግሎት የሚሰጥበት እኩልነትና ማሕበራዊ ፍትህ የሰፈነባት ማዕከል እንድትሆን ለማድረግ ከህብረተሰብ ጋር በአንድነት ለመስራት በመስማማት መድረኩ ተጠናቆልል ።
More Stories
መንግስት በፈጠራና ክህሎት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ሀገራዊ የጤና ፖሊሲ ከመከላከልባሻገር አክሞ መዳንን መሰረት ያደረገ ስራን መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
በኢራን ወደብ በደረሰ ፍንዳታ 25 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ