በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 29ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር አርሰናል በሜዳው ኢምሬትስ ቼልሲን አስተናግዶ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የአርሰናልን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ሚኬል ሜሪኖ በመጀመሪያው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከአስራ ሁለት ጨዋታዎች በኋላ የማዕዘን ምት ግብ አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በ58 ነጥብ 2ኛ ላይ ሲቀመጥ ቼልሲ በ49 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
በሌላ የሊጉ ጨዋታ ፉልሀም በሜዳው ክራቨን ኮቴጅ የሰሜን ለንደኑን ክለብ ቶተንሀም ሆትስፐርን አስተናግዶ 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
የፉልሀምን የማሸነፊያ ግቦች ሮድሪጎ ሙኒዝ እና ሴሴኞን በሁለተኛው አጋማሽ አስቆጥረዋል፡፡
የሊጉ ጨዋታ ምሽት 4 ሠዓት ላይ ቀጥሎ ሲደረግ ሌስተር ሲቲ በሜዳው ኪንግ ፓወር ማንቼስተር ዩናይትድን ያስተናግዳል፡፡
ኤፍ ኤም ሲ
More Stories
አርሰናል 5 ተጨዋቾችን ያስመረጠበት የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ 11 ይፋ ተደረገ
ብሩኖ ፈርናንዴዝ የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን አሸነፈ
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ማጣሪያ ቅድመ ዝግጅቱን ዛሬ ይጀምራል