ማሻ፣ ጥር 5፣ 2017 (ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ) በሚቀጥሉት ቀናቶች በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ አንጻራዊ የእርጥበት መጠንና የደመና ሽፋን መጨመር እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
በሚቀጥሉት ቀናቶች ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በጥቂት የመካለኛው፣ በምሥራቅ፣ በሰሜን ምሥራቅ፤ በሰሜን ምዕራብ እንዲሁም በደቡብ ኢትዮጵያ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ አንጻራዊ የእርጥበት መጠንና የደመና ሽፋን መጨመር እንደሚኖር የትንበያ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘም የደቡብ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ምዕራብ እና የምዕራብ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንሚያገኙም ነው የኢንስቲትዩቱ መረጃ የሚያመላክተው፡፡
በሌላ በኩል አሁን ላይ እየተስተዋለ ያለው የበጋው ደረቅ፣ ጸሀያማ እና ነፋሻማው የአየር ሁኔታ በሚቀጥሉት ቀናትም ቀጣይነት እንደሚኖረው አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ተብሏል፡፡
(ኤፍ ኤም ሲ)
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።