በጀርመን አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ በስፔን አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡ በበርሊን ኦሊምፒክ ስታዲየም በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ስፔን እንግሊዝን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለአራተኛ ጊዜ የዋንጫው ባለቤት ሆናለች፡፡ በጨዋታው የስፔንን የማሸነፊያ ግቦች ኒኮ ዊሊያም እና ማይክል ኦያርዛባል በ47ኛው እና በ86ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡ እንግሊዝን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ ተቀይሮ የገባው ኮል ፓልመር በ73ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡ በውድድሩ አስደናቂ ብቃት ሲያሳይ የቆየው የ17 ዓመቱ ኮከብ ላሚን ያማል በዚህም ጨዋታ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ በማቀበል ውድድሩን በስኬት አጠናቋል፡፡
EBC
More Stories
ኢትዮጵያዊ በዳምጠው ከበደ ተጨማሪ ሜዳሊያ አገኘች
ቴፒ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት
የኤሲሚላን የቀድሞ ተጫዋች ፍራንኮ ባሬዚ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ