የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የኦስትሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ሲሞን ክናፕ ጋር በኢትዮጵያና ኦስትሪያ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡
አምባሳደር ምስጋኑ የሀገራቱ ታሪካዊ ግንኙነት በተለያዩ መስኮች በተለይም በኢኮኖሚው ዘርፍ የበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
አምባሳደር ክናፕ በበኩላቸው÷ የኦስትሪያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲሁም የኦስትሪያ የቢዝነስ ልዑካን ቡድን በመጭው ጥቅምት ወር በኢትዮጵያ ጉብኝት ለማድረግ ያለውን እቅድ አብራርተዋል።
ሁለቱ ወገኖች በኦስትሪያ የንግድ ተቋማት እና በኢትዮጵያውያን አቻዎቻቸው መካከል የልምድ ልውውጥ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን መጠቆማቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የኢትዮጵያ ማዕድን ሚኒስቴርንና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በኦስትሪያ ከሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት ጋር በማስተሳሰር በማዕድን ዘርፍ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያንን አቅም ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ላይም ተወያይተዋል።
FBC
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ