ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላለፉ።
በህንድ በተካሄደው ምርጫ ለሶስተኛ ጊዜ ላሸነፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት፤ ምርጫ ህዝብ እውነተኛ የስልጣን ባለቤት መሆኑ የሚገለጥበት ነው ብለዋል።
ወዳጄ ናሬንድራ ሞዲ ሰላማዊ ምርጫ በማካሄድ ለድል በመብቃትዎ እንኳን ደስ ያለዎ በማለት ገልጸው፤ ምርጫው በህንድ የዴሞክራሲ ስርዓት እያበበ መምጣቱን የሚያመላክት መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።
በተመሳሳይ በደቡብ አፍሪካ ለተካሄደው ነጻ፣ ግልጽና ሰላማዊ ምርጫ ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው የምርጫ ሂደቱ የዴሞክራሲ መርሆዎችን ያከበረ መሆኑን ገልጸው፤ ይህ ደግሞ ለህዝብ ፍላጎትና ለዴሞክራሲ እሴቶች የመገዛት ቁርጠኝነት ነው ብለዋል።
FBC
More Stories
ኢራን የቻይናው ፕሬዚዳንት ያቀረቡትን ባለ አራት ነጥብ የሰላም የውሳኔ ሐሳብ እንደምትደግፍ ገለጸች
የኢትዮጵያ እና የተመድ የ80 ዓመታት ታሪካዊ ቁርኝት
ለ7ኛዉ ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ ይምረጡኝ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ በአንድራቻ ወረዳ ጌጫ ከተማ ተካሂደዋል ።