ጠፈርተኛው ከ2008 ጀምሮ 5 ጉዞዎችን ያደረገ ሲሆን በርካታ ቀናትን በህዋ ላይ በማሳለፍ ክብረወሰኑን ይዟል
አሜሪካ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ሩስያ በጠፈር ሳይንስ ላይ የሚያደርጉት ፉክክር እያደገ መጥቷል
ሩሲያዊው ጠፈርተኛ ኦሌግ ኮኔንኮ 1ሺህ ቀናትን በህዋ ላይ በማሳለፍ የመጀመርያው ሰው ተብሏል፡፡ ከ2008 ጀምሮ ወደ ህዋ መጓዝ የጀመረው ኮኔንኮ እስካሁን 5 ጉዞዎችን ወደ ጠፈር አድርጓል፡፡
ለመጨረሻ ግዜ በመስከረም 15 2023 ወደ ህዋ የተጓዘው ጠፈርተኛው ስራውን አጠናቆ ወደ ምድር የሚመለሰው በመጭው መስከረም 23 2024 ነው፡፡
ኮኔንኮ ወደ ምድር ሲመለስ እስካሁን በህዋ ከቆየባቸው ቀኖች ጋር ሲደመር በአጠቃላይ 1 ሺህ 110 ቀናትን በማሳለፍ የመጀመሪያው ሰው ይሆናል፡፡
ከዚህ ቀደም ረጅም ቀናትን በህዋ ላይ የቆየው ሌላኛው ሩስያዊ ጠፈርተኛ ጌናዲ ፓዳልካ ሲሆን ኮኔንኮ ባሳለፈነው ጥር ወር ላይ 878 ቀን ከ11 ሰአታት ከ29 ደቂቃ በመቆየት የዚህን ጠፈርተኛ ሪከርድ አሻሽሎታል፡፡
ጠፈርተኛው “ይህን አይነት ክብረወሰን በመያዜ ደስተኛ ነኝ በህዋ ላይ ይህን ያህል ጊዜ መቆየት ቀላል አይደለም ነገር ግን ስኬታማ በመሆኔ ደስተኛ ነኝ” ብሏል፡፡
አሜሪካ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ሩስያ ጠፈር ላይ የሚያደርጉት ፉክክር እያደገ መጥጧል፤ ሀገራቱ በግል እና በመንግስት ተቋማት የህዋ አዳዲስ ግኝቶችን በማስተዋወቅ እና የተለያዩ ሙከራዎችን በማድረግ እየተፎካከከሩ ይገኛሉ፡፡
Al-Ain
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች