ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢራኑ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በደረሰው አሰቃቂ የሄሊኮፕተር አደጋ ሕይወታቸውን ላጡት የኢራን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚር አብዱላሂ በኢትዮጵያ ሕዝብ፣ መንግስትና በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡ለፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲና አሚር አብዱላሂ ቤተሰቦች እንዲሁም ለኢራን ሕዝብና መንግስትም መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
FBC
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ